Child and adolescent counseling

Adolescent Counselling

 Adolescent counselling is a type of counselling with the intention of helping adolescents understand their feelings, changes and cope up with peer pressure. Adolescence is the stage when we make the transition from child to adult, this usually occurs between 10 and 19. In this time physical as well as psychological changes take place, the physical changes often referred to as puberty. Growing up is characterised by new experiences, which includes peer pressure; that comes truly into play and young people may first be exposed to drugs, alcohol or cigarettes. With all this temptation comes responsibility and it is the combination of the two which may cause frustration when going through puberty often results in psychological chaos.

Aha’s work with children and adolescent is mainly done in partnership with schools and parents. It ranges from assessment and diagnosis of learning difficulties, development disorders and behaviour related problems.

 

የልጆች እና የወጣቶች ምክክር አገልግሎት

ከልጅዎች ጋር ችግር አጋጥምዎት ለቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ መክረው አስመክረው ችግሩን መፍታት አልቻሉም?? እንግዲያውስ ወደ አሃ የስነ-ልቦና ማማከር ተቋም ብቅ ይበሉ፤

 የልጆች እና የወጣቶች የምክክር ዓይነት ወጣቶችን ወይም ደግሞ እድሜያቸው በጉርምስና ዘመን ላይ ያሉ እና ከቤተሰብ እና ከጓደኛ ጋር ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ውስጥ ያሉ ፣ አሉታዊ የሆነ የአቻ ለአቻ ግፊት ውስጥ የወደቁ እና የመሳሰሉትን ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ የሚሰጥበት የምክክር ዓይነት ነው፡፡ ጉርምስና በልጅነት እና በወጣትነት መካከል የሚገኝ የሽግግር ሲሆን ከ10 እስከ 19 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ነው፤  በዚህ ጊዜም  በአካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች ውስጥ ይታለፋል፤ አካላዊ ለውጡንም በተለምዶ ጉርምስና እንለዋለን፡፡

ማደግ (ጉርምስና) በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ያልፋል ከእነዚም መካከል ከላይ እንደተጠቀው የአቻ ለአቻ ግፊት በዋናነት ይጠቀሳል፤ በዚህም ልጆች (ወጣቶች) ለተለያየ አደንዛዥ ዕጾች የመጋለጥ እድላቸውን ሰፊ ያደርገዋል፡፡ የአሃ ስራም ከዚህ የተገናኘ ነው፤ ተቋሙ ከተለያዩ አጋር አካሎች ጋር ማለትም ከት/ቤቶች እና ቤተሰቦች ጋር በመተባር ከመማር ችግር ካለባቸው እስከ የባህሪ ችግር ያለባቸው ድረስ ሰፊ ስራ ይሰራል፡፡