There is no doubt that as an employer you need a well motivated and fresh employees, in being so, they would be productive. So keeping your employees active would benefit both parties, that's why organizational counseling plays a pivotal role here.
Often managers or owners of enterprises and companies neglect the importance of organizational counseling, but it should be one part of their task for the following advantage;
- - Workers satisfaction: providing periodic counseling service to employees results a motivated worker with the administration and working environment.
- - Promoting conducive working environment: Counseling helps workers to be free from stress and frustration and creating a good working environment between one another.
- - Motivate workers: with counseling employees would be motivated to conduct day to day activities.
- - Good relationship: Most of the time workers and managers (owners) see each other negatively, but counseling helps to improve this relationship for the good of all parties.
- - Effective resource utilization: organizational counseling indirectly promotes workers to effectively utilize the resource that they have at their disposal.
- - Developing sense of responsibility: one of the many objectives and importance of is developing sense of responsibility among employees.
- * Minimizing conflicts: disputes between workers endanger the productivity of workers and the organization in general, that's why organizational counseling is decisive.
- - Apply psychological researches in a work place
- - Understand customer’s behavior and needs.
የተቋማት የምክክር አገልግሎት
በተቋምዎ ወይም በደርጅትዎ ውስጥ ጥሩ ተነሳሽነት ያለው ሰራተኛ ማግኘት ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ መናገር ጉንጭ ማልፋት ነው፤ እናም እንደዚህ ዓይነት ሰራተኞች የድርጅትዎን ውጤታማት ከፍ እንደሚያደርጉት እሙን ነው፤ ለዚህ ደግሞ የተቋማት የምክክር አገልግሎት ከፍተኛ ድርሻውን ይይዛል፡፡
ብዙ ጊዜ አሰሪዎች የተቋማት የምክክር አገልግሎትን ችላ ሲሉ ይስተዋላል፤ ሆኖም ግን ይህ ጉዳይ ለነገ ይደር ተብሎ የማይቀመጥ እንደሆነ ከሚከተሉት ጥቅሞቹ መረዳት እንችላለን፤
- - የሰራተኞች እርካታ፡- ወቅቱን የጠበቀ የምክክር አገልግሎት ለስራውና እና ለአስተዳደሩ ከፍተኛ ተነሳሽነት ያላቸው ሰራተኞች እንዲኖሩ ይረዳል፤
- - መልካም የስራ ሁኔታ፡- የተቋማት የምክክር አገልግሎት ሰራተኞችን በተለያዩ ምክንያቶች ከሚመጡ ጭንቀቶች ነጻ በማድረግ ጥሩ የሆነ የስራ ሁኔታ እንዲኖር ያስችላል፡፡
- - ጥሩ የሰራተኞች መስተጋብር ፡- በብዛት በሰራተኛ እና ባሰሪዎች ወይም በተጨማሪም በሰራተኞች መካከል ሻካራ የሆነ ግንኙነት ሊኖር ይችላል፤ ስለዚህም ይህ ምክክር በመሀል የሚኖርን ግንኙነት ጠንካራ እና ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
- - ጥሩ የሀብት አጠቃቀም፡- የተቋማት የምክክር አገልግሎት ሰራተኞች ያላቸውን የሀብት አጠቃቀም እንዲስተካከል እና ጥሩ እንዲሆን ያግዛል፡፡
- - የኃላፊነት ስሜትን መጨመር፡- ይህ ዓይነቱ ምክክር ሰራተኞች ላይ የሚኖረውን ስራን በኃላፊነት መንፈስ የመስራት ስሜትን ይጨምራል፡፡
- - የተለያዩ ሳይንሳዊ የሆኑ የሥነ-ልቦና ጥናቶችን በስራ ቦታ ለመተግበር እና ውጤታማ ለመሆን ይረዳል፡፡
- - የደንበኞችን ባህርይ ለማጥናት እና ጠንቅቆ ለማወቅ ያግዛል፡፡