Psychological Assessment

Psychological assessment is the application of different tests and techniques to fully understand one’s personality, behavior and capabilities. Regarding Aha’s Psychologists, all we do is  take the information gathered from psychological assessment and blend it into a comprehensive and complete picture of the person tested. Our recommendations are based on all the outcomes  of the assessment and also from the interviews with friends, family, and other related parties who may provide the heads up on the person’s behavior in different settings.

Our psychological assessments are not based on one test, since every one of us has various competencies and limitations; we employ different techniques to fully understand the person being tested and reach at conclusions.

 

ስነ-ልቦናዊ ምዘና

ሰዎች በተደጋጋሚ ምን ዓይነት ሰው ነህ ለሚለው ጥያቄ፤ አላውቅም ወይም ደግሞ ይህን መመለስ ይከብደኛል ሲሉ ይደመጣሉ፤ ለዚህ መፍትሄው ቀላል ነው ስነ-ልቦናዊ ምዘና፡፡

ስነ-ልቦናዊ ምዘና የሰዎችን የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህርይ እንዲሁም ችሎታ ለማወቅ የተለያዩ ምዘናዎችን የምንጠቀምበት የስነ-ልቦና አንድ ዘርፍ ነው፡፡ የአሃ የስነ-ልቦና ባለሙያዎችም  ከእነዚህ ምዘናዎች በመነሳት ስለ አንድ ሰው ሙሉ የሆነ መረዳት እንድንይዝ ያደርጉናል፡፡ የባለሙያዎቹ ምክረ-ሃሳቦችም በምዘናዎቹ ውጤት ላይ መሰረት ያደረጉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ እንደ አስፈላጊነቱ ቤተሰብ፣ እንዲሁም ወዳጅ ዘመድን በማነጋገር ስለ ሰዎቹ ማንነት የሚነግረን ነገር ካለ መረጃዎች ይሰባሰባሉ በዚህም ሁሉን አቀፍ የሆነ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያስችላቸዋል፡፡ የተቋሙም (አሃ) ዋናው አላማ ምዘናዎቹ በአንድ መመዘኛ መንገድ ብቻ እንዳይከናወኑ ማድረግ ነው ምክንያቱም ሰዎች የተለያየ አቅም እና ችሎታ አላቸው ብሎ ስለሚያስብ የተለያዩ መመዘኛዎችን ይጠቀማል፡፡