Marriage and Family counseling

Marriage counseling or relationship counseling is an intervention that is carried out by licensed counselor. Aha’s primary goal is to help couples that are having difficulties in their relationship. Our organization can help married couples make thoughtful decisions, overcome differences and improve the relationship between them.

 Aha understands that when people seek marriage or couple counseling, it simply means that they are trying to change their relationship positively and possibly avoid separation or divorce by enhancing the way they communicate with each other, be open and honest with each other as well as learn to understand why they may be having difficulties in their relationship. The Counseling usually involves both partners, it helps couples to recognize underlying conflicts and improve their relationship. In general, marriage counseling encourages the parties to focus on self-improvement and self-awareness.

In a marriage or relationship counseling, our counselors can help you to:

  • - Identify your hopes, expectations and relationship concerns.
  • - Appreciate and understand each other better
  • - Enables you to communicate with each other effectively.
  • - Explain why there is difference in your opinion
  • - Discover different problem solving techniques
  • - Move on from conflicts in your marriage or relationship and open up a new chapter in your life.

To conclude, through our marriage and relationship counseling, our endeavor is to work with the family as a system or unit. It involves meeting with couples, the entire family or it could be various members of the family together who are pertinent to the nature of the problem. However bear in mind that marriage is not the requirement to get family or couples therapy, being in a relationship which is unhealthy is.

 

የትዳር፣ የፍቅር ግንኙነት እና የቤተሰብ ምክክር

አንዳንድ ጊዜ ትዳር እና ጾታዊ የፍቅር ግንኙነቶች አሰልቺ እነዲሁም አባጣ ጎርባጣ የበዛበት አልፎም ለፍቺ አልያም ለመለያት በማድረስ ቤተሰብን እሰከመበተን ድረስ ሊሄድ ይችላል፤ ግን ለምን ይሄ ሁሉ ነገር ይከሰታል እስኪ ቆም ብለን እናስብ፤ትዳርን ከመፍታት እና ልጆችን ከመደተን ሊታደግ የሚችል ነገር አለ፤ ምክክር፤ በትዳር እና በቤተሰብ ምክክር አዲስ እና ውጤታማ ህይወት መምራት እንችላለን፡፡

የትዳር ወይም የጥንዶች በባለሙያ የሚሰራ የምክክር ዓይነት ሲሆን፤ የተቋሙማችን (አሃ) ተቀዳሚ አላማም ባለ ትዳሮች እና ጥንዶች ያሉባቸውን ስነ-ልቦናዊ ችግሮችን ነቅሶ  በማውጣት ለችግሮቻቸው መፍትሔ መስጠት ነው፤ ይህንም የሚያደርገው  ሰዎች ወደ ተቋማችን ሲመጡም በመካከላችው ያለውን ችግር በማስወገድ እና ልዩነቶችን በማጥበብ፣ በመሀላቸው ያለውን ተግባቦት ማሳደግ፣ መተማመናቸውን መጨመር እና መለያየትን ለማስቀረት እንደሚመጡ በመረዳት ነው፡፡

ምክክር ሁልጊዜም ሁለቱንም (ጥንዶችን) አካላት ያካተተ ሂደት ነው፤ በዚህም በጥንዶች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲገነዘቡት እና እንዲፈቱት በማገዝ ራስን ማወቅን እና ራስን መሻሻል ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡

በትዳር፣ በፍቅር ግንኙነት እና በቤተሰብ ምክክር፣ ባለሙያዎች የሚከተሉትን ያደርጋሉ፤

  • - ወደፊት በግንኙነታቸው ውስጥ ምን እንደሚጠብቃቸው እና ተስፋቸውን እንዲለዩ ይረዷቸዋል፤
  • - በመሀላቸው ያለው ተግባቦት እና ክብር ከፍ እንዲል ያግዛሉ፤
  • - የበለጠ እንዲወያዩ እና እንዲያወሩ ያደርጋሉ፤
  • - በጥንዶች መሀል የሚፈጠር ልዩነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ይለያሉ፤
  • - የተለያዩ ችግሮችን መፍቺያ መንገዶችን ጥንዶችን ያስገነዝባሉ፤
  • - ከግጭቶች በማለፍ ጥንዶች የተሻለ እና ውጤታማ ኑሮ እንዲኖሩ ያስችላሉ፤

ለማጠቃለል፤ በጥንዶች እና በቤተሰብ ምክክር የአሃ ፍላጎት ቤተሰብን እንደ አንድ ትልቅ ተቋም አድርጎ መስራት ነው፤ በዚህም ጥንዶችን እና እንደ አስፈላጊነቱ የቤተሰቡን አባላት በማግኘት ችግሮችን በመለየት ላይ ይሰራል፤ ይህን ስንል ግን የግድ ስነ-ልቦናዊ ችግር ያለባቸው ጋብቻ ላይ ያሉ ጥንዶች ብቻ ምክክሩ ያስፈልጋቸዋል እያልን እንዳልሆነ ልብ ይሏል፤ ማንኛውም የፍቅር ግንኙነት እና ቤተሰብ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ እያለፈ ከሆነ ምክክሩ ወሳኝ ነው፡፡